Home ሳይ-ቴክ AIን ስነምግባር በተሞላበት መንገድ ለመጠቀም እንድንችል፣ የአጠቃቀም ፖሊሲና መመሪያ ያስፈልገናል፡፡ AIን አትጠቀም ብሎ መከልከል መፍትሔ አይሆንም ” -ዶ/ር ደረጄ እንግዳ

AIን ስነምግባር በተሞላበት መንገድ ለመጠቀም እንድንችል፣ የአጠቃቀም ፖሊሲና መመሪያ ያስፈልገናል፡፡ AIን አትጠቀም ብሎ መከልከል መፍትሔ አይሆንም ” -ዶ/ር ደረጄ እንግዳ

by admin

የቻይናው ሁዋዌ ተክኖሎጂስ፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት / AI ቴክኖሎጂን በትምህርት ዘርፍ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚመክር ስበሰባ በትላንትናው ዕለት አካሂዶ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተከታተለው በዚህ የውይይት በመድረክ የAI ቴክኖሎጂን በተለይም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለማስፋፋት የተለያዩ ችግሮች መኖራቸውን ተነስቷል።

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕረዝደንት የሆኑት ዶ/ር ደረጄ እንግዳ ፦
– በገጠርም ሆነ በከተማ ኤአይን ለመጠቀም የመሰረተልማት አለመስፋፋት፤
– የሰለጠነ የሰው ሀይል እጥረት፤
– የተሰጥኦ ማነስ፤
– የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍልሰት ተግዳሮት መሆኑን አንስተዋል።

” አሁን ከቴክኖሎጂው እያገኘን ያለነው ጥቅም ምናልባትም ከጎግል የተለየ አይደለም ከዚያ ባሻገር ልንጠቀምበት ይገባል ” ሲሉ ጠቁመዋል።

” በትምህርት ዘርፉ በዩኒቨርሲቲዎች ያሉንን መምህራን ማሰልጠንና ማብቃት አለብን ” ያሉት ዶ/ር ደረጄ ” AIን ስነምግባር በተሞላበት መንገድ ለመጠቀም እንድንችል፣ የአጠቃቀም ፖሊሲና መመሪያ ያስፈልገናል፡፡ AIን አትጠቀም ብሎ መከልከል መፍትሔ አይሆንም ” ብለዋል።

” ስርዓተ ትምህርታችንን/ካሪኩለሙን መከለስ አለብን፣ ስርዓተ ትምህርቱ ራሱ ለዚህ የሚያመች አይደለም፡፡ ባለፉት ሶስትና አራት አመታት በኤአይ ዘርፍ ብዙ ለውጦት ቢኖሩም ይህንን ወደ ትምህርት ስርዓቱ ማካተት አልተቻለም፡፡ አንዱና ትልቁ እንቅፋት እሱ ነው ” ሲሉ ነው የገለጹት።

ተማሪዎቻችንን የምንመዝንበት መንገድም ዳግም መታየት አለበት ያሉት ፕረዚዳንቱ ” ብዙ ፈተናዎች አሉን፣ ግን ይህንን ተቋቁመን ወደፊት መግፋት አለብን፡፡ ኤአይን ለማስፋፋት በጣም ግዙፍ የሆነ ኢንቨስትመንት ይፈልጋል፣ ትልቅ የአስተሳሰብ ለውጥም ያስፈልጋል ” ነው ያሉት።

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕረዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ በበኩላቸው ኤአይን በመጠቀሙ ሒደት የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።

በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያለውን የኤአይ አጠቃቀምን ስናስብ፣ ባልተገባ መንገድ የመጠቀሙ ነገርም አብሮ መታሰብ አለበት ያሉት ዶ/ር ጀማል፣ ይህ በጣም አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል በማለት ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡

ስርዓተ ትምህርቱ በፅንሰ ሀሳብ ላይ የተንጠለጠለ ነው ያሉት ዶ/ር ጀማል ተስጥኦን ማበልፀግ ከህፃናት መጀመር አለበት፡፡ ህፃናትን በኤአይ ዘርፍ ማነሳሳት አስፈላጊ ነው፡፡ ከዛም በትምህርት ቤቶችና በዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ ግንዛቤውን ማስፋት ተገቢነት አለው ሲሉ ተናግረዋል።

አጋራ

ተዛማጅ ልጥፎች

Leave a Comment

አንደበት

ለተጠቃሚዎች የቅርብ ጊዜ አካባቢያዊ እና ዓለም አቀፍ ዜና  በማቅረብ ለአንባቢዎች የተሟላ መድረክ የሚሰጥ ዜና ጣቢያ ለአንባቢ ምቹ በይነገጽ እና ሰፋ ያለ የዜና ምድቦች አማካኝነት እንደ ፖለቲካ, ቴክኖሎጂ, መዝናኛ, ስፖርት እና ሌሎችም ባሉ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ወቅታዊ ዜናዎችን ያቀርባል፡፡

ጋዜጣ

አዳዲስ ዜናዎች በቅድሚያ እንዲደርሶት ኢሜሎን በማስገባት ይመዝገቡ

የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

@2025 – All Right Reserved.  Powered by Ewenet Communication