Home መዝናኛ 2ኛው ዙር የስታር ዋይድ አዋርድ ሽልማት ሊካሄድ ነው

2ኛው ዙር የስታር ዋይድ አዋርድ ሽልማት ሊካሄድ ነው

by admin

 

“ምስጋናን ባህላችን እናድርግ” በሚል መሪ ቃል 2ኛው ዙር ስታር ዋይድ አዋር የሽልማት ስነ ስርዓት በከለር ፊል ኢቨንት ኦርጋናይዘር አዘጋጅነት የፊታችን ግንቦት 2017 በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል። በሀርመኒ ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የስታር ዋይድ አዋርድ ስራ አስፈፃሚ አሳንቴ ስሜ የስታር ዋይድ አዋርድ ፕሮሞተር አንጋፋው ጋዜጠኛ ሽመልስ በቀለ ከአባይ ቴሌቨዥን ተወካይ አቶ ዜማ ያሬድ እንዲሁም የሚድያ ባለሙያዎች ታድመዋል። ለህዝቦቻቸው በጎ ነገር ላበረከቱ ግለሰቦች ሽልማት በመስጠት ይታወቃል ካለፈው አመት ጀምሮ ለግለሰቦች ለድርጅቶች እና ለተቋማት ምስጋና እውቅናና ክብር በመስጠት ላይ ይገኛል። ተሸላሚዎችን ለመምረጥ ከልዩ ልዩ መስክ ዳኞች እየተመረጡ ይገኛሉ። ለሽልማቱ የሚበቁ አሸናፊዎች ከዳኞች ባሻገር ህዝብ ድምፅ እንዲሰጥ ድረ-ገፅ ተከፍቷል። ስታር ዋይድ አዋርድ ከአእምሮ ጥበቃ ባለስልጣን እውቅና ያገኘ ሲሆን ከመንግስት አካል እውቅና ተሰጥቶት የሚሰራ የሽልማት ድርጅት ነው። የ2017 የሽልማቱ አሽናፊዎች በመጪው ግንቦት ተለይተው ይታወቃሉ።

አጋራ

ተዛማጅ ልጥፎች

Leave a Comment

አንደበት

ለተጠቃሚዎች የቅርብ ጊዜ አካባቢያዊ እና ዓለም አቀፍ ዜና  በማቅረብ ለአንባቢዎች የተሟላ መድረክ የሚሰጥ ዜና ጣቢያ ለአንባቢ ምቹ በይነገጽ እና ሰፋ ያለ የዜና ምድቦች አማካኝነት እንደ ፖለቲካ, ቴክኖሎጂ, መዝናኛ, ስፖርት እና ሌሎችም ባሉ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ወቅታዊ ዜናዎችን ያቀርባል፡፡

ጋዜጣ

አዳዲስ ዜናዎች በቅድሚያ እንዲደርሶት ኢሜሎን በማስገባት ይመዝገቡ

የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

@2025 – All Right Reserved.  Powered by Ewenet Communication