#Ethiopia | የቻይናዋ ሙሽሪት ከሠርጓ ቀን በፊት ማልቀስ መለማመዷና የሰርጓ ቀን ስቅስቅ ብላ ማልቀሷ ነገሩን “ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ” ከሚለው ከፍ አድርጎታል፡፡
በቻይና የቱጂአ ማህበረሰብ አባል የሆነች ሙሽራ እናቷ፣ ሴት አያቷ እና ሌሎች የቤተሰብ አባላትም እያገዟት ሰርጓን ለማሳመር ታለቅሳለች ይለናል የስኬድ ላይን ድረ ገፅ መረጃ፡፡
ነገር ግን ለቅሶ ለደቂቃዎች ወይም ለሰዓታት ብቻ የሚቆይ ሳይሆን የሰርጉ ቀን ገና አንድ ወይም ሁለት ወር እየቀረው ነው ማልቀስን መለማመድ የሚጀመረው።
ሙሽሪት ማልቀስ በጀመረች 10ኛው ቀን እናቷ በቀጣዩ 10ኛ ቀን ደግሞ ሴት አያቷ፣ እህቶቿ፣ አክስቶቿ እና በመንደሩ በሰርግ ወቅት ለቅሶ የተካኑ ናቸው የሚባሉ ሴቶች የለቅሶ ልምምዱ አካል ናቸው።
በተለይም ሙሽሪት የሰርጓ እለት ለአንድ ሰዓት ያህል በሰርጉ ታዳሚዎች ፊት ስቅስቅ ብላ በማልቀስ ሰርጓን ታደምቀዋለች፡፡
የለቅሶ መነሻ ምክንያት ደግሞ በጥንታዊት ቻይና ባህል ሙሽሪት ከወላጆቿ ቤት በትዳር ወደ አዲሱ የትዳር አጋሯ ጋር መሄድን በማስመለከት የሚደረግ ነው።