13
በዚህም ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ባለፈው አርብ በስቅለት ዕለት በፎኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በቅድስት ድንግል ማርያም ዙሪያ ያስተላለፉትን ትምህርት በተመለከተ ውይይት አድርጓል።
በብፁዕነታቸው የተላለፈውን ትምህርት ዝርዝር ሁኔታን በመመርመርም ውሳኔ ለማስተላለፍ ይቻል ዘንድ ሁሉም የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በምልዓት በተገኙበት ለረቡዕ ሚያዝያ 22 ቀን
2017 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል።
በሌላ በኩል ፤ በካቶሊክ መሪ በነበሩት ብጹዕ ወቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሥርዓተ ቀብር ላይ ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በምሥራቅ ጎጃም እና በአውሮፓ ጀርመን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የጣልያንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቤተክርስቲያኗን በመወከል እንዲገኙ ተወስኗል።