ከ6 እስከ 9 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ባለመከፈሉ ምክንያት ሥራ ማቆማቸውንና 14 ሰዎች መታሰራቸውን በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሎካ አባያ ወረዳ የሚገኘዉ ሀንጣጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጤና ባለሞያዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል።
ጤና ባለሙያዎቹ ዛራ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ከታሰሩት 14 ባለሙያዎች 7ቱ ሲፈቱ 7ቱ አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ ብለዋል።
ካልተከፈለዉ የ9 ወራት ዉዝፍ ዉስጥ የ4 ወራት ክፊያ መፈጸሙን ተከትሎ ሥራ መጀመራቸውን የገለጹት ባለሞያዎቹ ” የትርፍ ሰዓት ስራ ከቆመ በኋላ ክፍያ መፈፀም በወረዳዉ የተለመደ ጉዳይ ነዉ ” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
ከታሰሩ 5ኛ ቀናቸዉን የያዙት የታሰሩ የጤና ባለሙያዎች ” እንዲፈቱ በተደጋጋሚ እየጠየቅን ነዉ ያሉት ሰራተኞቹ እስካሁን ግን ግልፅ ምክንያት አልተነገረንም ” ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሎካ አባያ ወረዳ አስተዳዳሪና ፖሊስ አዛዥን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። በጉዳዩ ላይ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆኑ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል።