#Ethiopia | አሜሪካ በቻይና የሚነሳውን ፈተና ለመጋፈጥ ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር አለባት ሲሉ የአሜሪካ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኩርት ካምቤል ተናገሩ ፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ ቻይናን በራሷ መግጠም እንደማትችል እና እንደ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ ካሉ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር እንዳለባት አመላክተዋል፡፡
ካምቤል፤ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እየተተገበረ ባለው “አሜሪካ ፈርስት” የሚል የውጭ ፖሊሲ ከቻይና ጋር በመጋፈጥ ለውድቀት እየተዘጋጀች ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ዋሽንግተን እና ቤጂንግ ከቴክኖሎጂ እስከ ንግድ ብሎም እስከ ወታደራዊ ብቃት ድረስ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ማንኛውንም ፈተና ለመቋቋም የሚያስችል የኢንዱስትሪ እና የቴክኖሎጂ አቅም ያላት ቢሆንም ቻይና በቴክኖሎጂ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በመርከብ ግንባታ እና በወታደራዊ መስኮች በኩል በርካታ ስራዎች መሰራቷን አንስተዋል፡፡
በመሆኑም ዩናይትድ ስቴትስ ይህንን ፈተና ብቻዋን ልትቋቋም እንደማትችል አንስተው፤ እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቋቋም ብቸኛው መንገድ ከአጋሮች ጋር በቅርበት መስራት ነው ብለዋል።