#Ethiopia | ፈረንሳይ የተጠቃሚዎችን መረጃ ያለምስጥራዊ የይለፍ ቃል በድብቅ ለማግኘት የምታስገድድ ከሆነ ቴሌግራም ፈረንሳይን ለመልቀቅ ይገደዳል ሲል የቴሌግራም መስራችና ባለቤት ፓቬል ዱሮቭ ተናገረ፡፡
ኩባንያው የተጠቃሚዎችን ሰብዓዊ መብት በመገርሰስ የግል መረጃዎቻቸውን ያለፍቃዳቸው በድብቅ ሶስተኛ ወገን እንዲያገኘው ከመፍቀድ በፈረንሳይ ያለውን የማህበራዊ ሚዲያ ገበያ ለመልቀቅ እንደሚመርጥ ገልጿል፡፡
የፈረንሳይ ብሄራዊ ምክር ቤት ባለፈው ወር የዜጎችን የግል መረጃ ያለፍቃዳቸው ሌላ ሰው እንዳይመለከት ያላቸው መብት ለማገድ የተዘጋጀውን ህግ ውድቅ ማድረጉ ምክር ቤቱ ትክክለኛ ውሳኔ መወሰኑን ፓቬል ጠቅሷል፡፡
ቴሌግራምን የሚጠቀሙ የአደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪዎችን ለመቆጣጠር በሚል ፈረንሳይ ያዘጋጀችው ረቂቅ ህግ፤ ወንጀሉን መቆጣጠር እንደማያስችልና ተጠርጣዎች ሌሎች አነስተኛ መተግበሪያዎችን በመጠቀም ተመሳሳይ ወንጀል ሊሰሩ እንደሚችሉ ተናግሯል፡፡
የቴሌግራም ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም የአደንዛዥ እፅ ዝውውር ወንጀል የሚሰሩ አካላትን ለመቆጣጠር የአውሮፓ ህብረት የዲጅታል አገልግሎት ህግን በማይቃረንና የፍርድ ቤት ትዝዛዘን በተከለ መንገድ የተጠርጣሪ ወንጀለኞችን አይፒ አድራሻና የስልክ ቁጥር ይፋ ማድረግ እንደሚቻል ገልጿል፡፡
ቴሌግራም የተጠቃሚዎችን የግል መረጃ ያለፍቃዳቸው ሌላ ሰው እንዳይመለከትና የመረጃ ደህንነት ለመከላከል ይሰራል ያለው የኩባንያው መስራች፤ ውሳኔው ወንጀለኞችን ለመጠበቅ አለመሆኑን የህግ አውጪዎች እንዲረዱ ማስረዳታችንን እንቀጥላልን ሲል መናገሩን ቴክሴንትራል ዘግቧል፡፡