Home ዜና ሚስቱን ገድሎ ሊሰወር የሞከረዉ ግለሰብ በፖሊስና በሕብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ሊዉል ችሏል ” – የጋሞ ዞን ፖሊስ

ሚስቱን ገድሎ ሊሰወር የሞከረዉ ግለሰብ በፖሊስና በሕብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ሊዉል ችሏል ” – የጋሞ ዞን ፖሊስ

by admin

በአርባ ምንጭ ከተማ ባለቤቱ ገድሎ ሊሰወር የነበረ ግለሰብ መያዙን ፖሊስ ገልጿል።

የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ሬታ ተክሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመዉ አርባ ምንጭ ከተማ ወዜ ቀበሌ ግድብ ሠፈር ነው።

ኮማንደር ሬታ ፤ የገዛ ባለቤቱን በመሳሪያ ተኩሶ በመግደል ሊሰወር የሞከረዉ ተጠርጣሪ በሕዝቡና በፖሊስ ትብብር በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል።

ተጠርጣሪው አቶ ነብዩ ጌታቸው ኤፍሬም እንደሚባልና ከሟች ጋር በትዳር ዓለም አብረዉ እንደነበሩ በመካከላቸዉ በነበረው አለመግባባት ሟች ወላጆቿ  ጋር በመሄድ ላለፉት 5 ወራት ከቤተሰቦቿ  ጋር ትኖር እንደነበር ገልፀዋል።

በትናትናዉ ዕለት ተጠሪጣርዉ አስቦና አቅዶ ጧት 4 ሰዓት ገደማ ” ላናግርሽ እፈልጋለሁ ” በማለት ካስጠራት በኋላ ሰዉ የማያይበትን ሁኔታ በማመቻቸት በሽጉጥ አንገቷ ስር ደቅኖ ተኩሶ እንደ ገደላት አስረድተዋል።

በኃላም ለመሸሸግና ለመሰወር ሲሞክር  በፖሊስ ክትትልና በሕብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ዉሎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ተጠርጣሪዉና ሟች በትዳር አብረዉ በነበሩበት ወቅት አንድ ልጅ አፍርተዉ እንደነበርም የፖሊስ መረጃ ያመለክታል።

ተጠርጣሪዉ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመበትን ሽጉጥ ወንዝ ዉስጥ እንደጣለ ቢገልፅም ፖሊስ ባደረገዉ ማጣራት ከደበቀበት በኤግዚቢትነት ይዞታል።

አጋራ

ተዛማጅ ልጥፎች

Leave a Comment

አንደበት

ለተጠቃሚዎች የቅርብ ጊዜ አካባቢያዊ እና ዓለም አቀፍ ዜና  በማቅረብ ለአንባቢዎች የተሟላ መድረክ የሚሰጥ ዜና ጣቢያ ለአንባቢ ምቹ በይነገጽ እና ሰፋ ያለ የዜና ምድቦች አማካኝነት እንደ ፖለቲካ, ቴክኖሎጂ, መዝናኛ, ስፖርት እና ሌሎችም ባሉ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ወቅታዊ ዜናዎችን ያቀርባል፡፡

ጋዜጣ

አዳዲስ ዜናዎች በቅድሚያ እንዲደርሶት ኢሜሎን በማስገባት ይመዝገቡ

የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

@2025 – All Right Reserved.  Powered by Ewenet Communication