#Ethiopia | ለአንድ ሳምንት ተልከው በቴክኒክ ችግር ለዘጠኝ ወራት ጠፈር ላይ ተንሳፈው የቆዩት ጠፈርተኞች ወደ ምድር ተመለሱ
አሜሪካዊያኑ ጠፈርተኞች ባሪ ዊልሞር እና ሱኒታ ዊሊያም በጎርጎሪያኑ ሰኔ 2024 ዓ/ም ለስምንት ቀናት ተልዕኮ ወደ ዓለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ ተጉዘው ነበር።
ነገር ግን ጠፈርተኞቹ የተጓዙበት የስታርላይነር መንኮራኩር በገጠመው የቴክኒክ ችግር በጣቢያው ከዘጠኝ ወራት በላይ እንዲቆዩ ተገደዋል። በዛሬው ዕለት ግን ኬኔዲ የጠፈር ጣቢያ መድረሳቸው ተዘግቧል።
ሁለቱም ጠፈርተኞች ልምድ ያላቸው የጠፈር ተመራማሪዎች ሲሆኑ፤ ከአሁኑ ከተልዕኮ በፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ ቀናትን በጠፈር አሳልፈዋል ተብሏል።
በተለይ የስታርላይነር በረራ የመጀመሪያ እና የሙከራ ተልእኮ ስለነበር ለከፋ ሁኔታ ተዘጋጅተው የሰለጠኑ ናቸውም ነው የተባለው።
ያም ሆኖ የናሳ ጠፈርተኞች ባሪ “ቡች” ዊልሞር እና ሱኒታ “ሱኒ” ዊልያምስ ከታሰበው በላይ ጠፈር ላይ በመቆየታቸው የጤና አደጋዎች ሊያጋጥሟቸው እንደሚችል ተነግሯል።