Home ዜናፖለቲካ የበዓል ገበያዉ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በማሳየቱ መሸመት ከአቅማችን በለይ ሆኗል ” – የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች

የበዓል ገበያዉ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በማሳየቱ መሸመት ከአቅማችን በለይ ሆኗል ” – የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች

by admin

በዓሉን ታሳቢ በማድረግ  በቂ ምርት ለማቅረብ ተሞክሯል ” – የከተማዉ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ

መጪዉን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ በሁሉም ምርቶችና ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የተባለ የዋጋ ጭማሪ ማስተዋላቸዉን የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ ” በቀናት ልዩነት ዉስጥ በእያንዳንዱ የሸቀጥና ሌሎች ለበዓሉ አስፈላጊ የሚባሉ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የተባለ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል ” ብለዋል።

ለአብነትም ፦

  • እንቁላል ከ13 እና 15 ወደ 20 ብር
  • ሽንኩርት በኪሎ ከ45 ወደ 70 እና 80
  • ቅቤ በኪሎ ከ800 ወደ 1000 ብር
  • ቲማቲም በኪሎ ከ40 ወደ 65
  • ዶሮ አንዱ ከ500-650 ወደ 850-1000
  • ስኳር በኪሎ ከ110 ብር ወደ 650 ብር
  • በርበሬ በኪሎ ከ600 ወደ  800 ብር
  • ዘይት የሚረጋ የሚባለው
                 ° 20 ሊትር ከ4500 ወደ 6200
                 ° 5 ሊትር ከ1200 ወደ 1600
                 ° 3 ሊትር ከ800 ወደ 1050
  • ዘይት ባለ ሃይላንድ
                 ° 5 ሊትር ከ1400 ወደ 1750
    እየተሸጡ መሆኑንና የጤፍ እና የምስር ዋጋ በአንፃሩ መጠነኛ የዋጋ ቅናሽ ማሳየቱን ገልፀዋል።

አስፈላጊዉ ቁጥጥር ካልተደረገ እስከ በዓሉ መዳረሻ ቀናት የዋጋ ጭማሪዉ ከዚህም ሊበልጥ እንደሚችል የሚናገሩት ሸማቾቹ በበዓሉ ዋዜማ ቀናት ዋጋ ለመጨመር ምርት የሚሰዉሩና እያሉ ” የለም ” የሚባሉ ሸቀጦችና ምርቶች ስለመኖራቸዉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የሀዋሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ ” ለበዓሉ አስፈላጊ የሚባሉ ልዩ ልዩ የጥራጥሬ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ የሸቀጥና ቅመማ ቅመሞች እጥረት እንዳይኖር በማህበራት ዩኒየኖች አማካኝነት በቂ ምርት ለማቅረብ ተሞክሯል ” ያለ ሲሆን ” የዋጋ ጭማሪዎች እንዳይኖር አስፈላጊውን የቁጥጥር ስራ እያከናወንኩ ነዉ ” ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸዉ አንዳንድ ጅምላ አቅራቢ ነጋዴዎችና ማህበራት የተወሰኑ ነጋዴዎችና ድርጅቶች ምርት የማሸሽና በየመደበቅ ስራ እየሰሩ መሆኑንና ለተጠቃሚው ሕብረተሰብ ብቻ መሸጥ የሚገባቸዉ ማህበራትም ለቸርቻሪ ነጋዴዎች እያሰራጩ መሆኑን ገልፀው ቁጥጥር እና ክትትሉ ካልተጠናረ የበዓል ገበያዉ ከዚህም በላይ ታይቶ የማይታወቅ የዋጋ ጭማሪ ሊታይበት ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል።

አጋራ

ተዛማጅ ልጥፎች

Leave a Comment

አንደበት

ለተጠቃሚዎች የቅርብ ጊዜ አካባቢያዊ እና ዓለም አቀፍ ዜና  በማቅረብ ለአንባቢዎች የተሟላ መድረክ የሚሰጥ ዜና ጣቢያ ለአንባቢ ምቹ በይነገጽ እና ሰፋ ያለ የዜና ምድቦች አማካኝነት እንደ ፖለቲካ, ቴክኖሎጂ, መዝናኛ, ስፖርት እና ሌሎችም ባሉ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ወቅታዊ ዜናዎችን ያቀርባል፡፡

ጋዜጣ

አዳዲስ ዜናዎች በቅድሚያ እንዲደርሶት ኢሜሎን በማስገባት ይመዝገቡ

የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

@2025 – All Right Reserved.  Powered by Ewenet Communication