Home ዜና “ለመንገድ ስራ የተከማቸ አፈር በህፃናት ላይ ተደርምሶ የአንድ ታዳጊ ሕይወት አጥፍቷል ” – የወላይታ ከተማ ፖሊስ

“ለመንገድ ስራ የተከማቸ አፈር በህፃናት ላይ ተደርምሶ የአንድ ታዳጊ ሕይወት አጥፍቷል ” – የወላይታ ከተማ ፖሊስ

by admin

በወላይታ ሶዶ ከተማ መርካቶ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ ለመንገድ ስራ ተብሎ የተከማቸ አፈር በአካባቢው ሲጫወቱ የነበሩ ሕፃናት ላይ ተደርምሶ የአንድ ታዳጊ ሕይወት ማለፉን የከተማው ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ሀብታሙ አስፋዉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አደጋዉ የተከሰተው በትናትናዉ ዕለት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አከባቢ መሆኑን የገለፁት አዛዡ በስፍራው የነበሩት ከ7 እስከ 9 ዓመት የዕድሜ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ሶስት ሕፃናት እንደነበሩ ተናግረው ሕይወቱ ካለፈዉ ታዳጊ በስተቀር በሌሎቹ ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን ገልጸዋን።

ሕፃናቱ እየተጫወቱ የነበረበት ቦታ ለአደጋ ተጋላጭ መሆን እየጣለ ካለዉ ከባድ ዝናብ ጋር ተዳምሮ ለአደጋዉ መከሰት መንስኤ ሆኗል ሲሉ አስረድተዋል።

ምክትል ኮማንደር ሀብታሙ አስፋው ፥ መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እንደሚሰራና በሶዶ ከተማ አስተዳደር የዉስጥ ለዉስጥ የአስፋልት መንገድ ስራ እያከናወነ የሚገኘዉ የቻይና ተቋራጭም አደጋ ሊያስከትሉ በሚችሉ ቦታዎችን ጥበቃ እንዲያስቀምጥ ትዕዛዝ እንደሚሰጥ አስታዉቀዋል።

ከአደጋው ጋር ተያይዞ በአንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ከአስር በላይ ሕፃናት ሕይወት እንዳለፈ ተደርጎ የሚሰራጨዉ መረጃ ከእዉነት የራቀ ነዉ ያሉት ፖሊስ አዛዡ እንደዚህ ዓይነት መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

አጋራ

ተዛማጅ ልጥፎች

Leave a Comment

አንደበት

ለተጠቃሚዎች የቅርብ ጊዜ አካባቢያዊ እና ዓለም አቀፍ ዜና  በማቅረብ ለአንባቢዎች የተሟላ መድረክ የሚሰጥ ዜና ጣቢያ ለአንባቢ ምቹ በይነገጽ እና ሰፋ ያለ የዜና ምድቦች አማካኝነት እንደ ፖለቲካ, ቴክኖሎጂ, መዝናኛ, ስፖርት እና ሌሎችም ባሉ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ወቅታዊ ዜናዎችን ያቀርባል፡፡

ጋዜጣ

አዳዲስ ዜናዎች በቅድሚያ እንዲደርሶት ኢሜሎን በማስገባት ይመዝገቡ

የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

@2025 – All Right Reserved.  Powered by Ewenet Communication