Home ዜና ታፍሰው የተወሰዱ አሉ። 20 ተማሪዎች በፓትሮል ተጭነው ተወስደዋል ፤ የት እንዳደረሷቸው አናውቅም ” – የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች

ታፍሰው የተወሰዱ አሉ። 20 ተማሪዎች በፓትሮል ተጭነው ተወስደዋል ፤ የት እንዳደረሷቸው አናውቅም ” – የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች

by admin

የመውጫ ፈተና ተፈትነው አልፈው ቴምፖራሪ ሲጠባበቁ እንደነበሩ የገለጹ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች፣ በድጋሚ ገና በሰኔ ላይ ‘ትፈተናላችሁ’ በመባላቸው ዛሬም መብታቸውን ሊጠይቁ በተዘጋጁበት በጸጥታ አካላት ድብደባና አፈሳ እንደደረሰባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬስ ምን አሉ ?

አንዱ ምሩቅ በሰጡን ቃል፣ ” ተማሪ ሲያልፍ እንዴት እንዲህ ተብሎ ይጠየቃል ? ብለን ሀሳብ ልናቀርብ በተሰለፍንበት ወቅት (50 እናሆናለን)፤  20 ተማሪዎች በፓትሮል ተጭነው ተወስደዋል፤ የት እንዳደረሷቸው አናውቅም። ስልካቸው አይሰራም። የቀሩትም ተደብድበው ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው አሉ ” ሲል ተናግሯል።

ሌላኛው ቅሬታ አቅራቢ ተመራቂ፣ ” ፈተናችን ታግዶ ከቆዬ ሰነባብቷል። በዚህም የግቢው አስተዳደር አካላትን ምላሽ ለመጠየቅ እየሞከርን ነበር። ሊያናግሩን ፈቃደኞች አይደሉም። ትላንት ልንጠይቅ ስሄድ አባረሩን፤ ዛሬ ልጠይቅ ስንሄድ ደግሞ በርካታ የጸጥታ አካላት ተጭነው መጥተው ተማሪዎች ተደብድበዋል። ሌሎችም በፓትሮል ተጭነው ወደ ማረሚያ ቤት ሂደዋል ” ብሏል።

ሌላኛው ቅሬታ አቅራቢ፣ ” የመወጫ ፈተና በድጋሜ ከጥር 25 እስከ 30 2017 ዓ/ም እንደወሰድን ይታወቃል። እንዳለፍን፣ ውጤት እንደመጣ ተልኮልናል። ፎቶ ተነሱ ተብለን ዶክሜት ልንሰጥ ፎቶ ተነስተን አስገብተን ክሊራስ የመውጫ ሞልተን ጨርሰን በሳምንቱ ውጤታችሁ ታግዷል ተባልን ” ሲል ገልጿል።

” ምንድነው ? አልን ‘ ትምህርት ሚኒስቴር ነው ያገደው ‘ ተባልን ስንጠብቅ ቆየን ነገር ግን እስከዛሬ የተሰማ ነገር የለም። የድሀ ልጆች ነን። ቤት ተከራይተን ለምግብ እያስላክን ነው። እኔ 25 ሺሕ ብር ወጪ አድርጌያለሁ። ዩኒቨርሲቲው ከግቢው አሶጥቶናል የሚሰጠን ሰርቪስ የለም ” ሲል ገልጿል።

ሌላኛዋ ተመራቂ ተማሪ፣ “ ተሰብስበን ጥያቄ ልንጠይቅ ነበር። እዚሁ እኛ ፊት ነው የደበደቧቸው። ወደ 20 ሴቶችም ወንዶችም የታሰሩ አሉ። የጸጥታ አካላት ሙሉ ግቢውን አጥለቅልቆት ነበረ ገና ማውራትና መጠየቅ ሳንጀምር ” ብላለች።

” ምንም ብጥብጥ አልፈጠርንም፤ ያወክነው ነገርም የለም፤ መብታችን እንዲከበርልን እሱም ኢ – ፍትሃዊ የሆነ ነገር ተደርጎብናል ፍትህ እንፈልጋለን ባልንበት ሁኔታ ነው ” ይህ ሁሉ የተደረገው ብላለች።

” ገና እየተሰባሰብን ባለበት መሳሪያ ታጥቀው ዱላ ይዘው የመጡ የጸጥታ ኃይሎች ሰበሰቡንና ተማሪዎቹን በግፍ እየደበደቡ ነበረ። አወላላ ሜዳ ላይ ታፍሰው የተወሰዱ አሉ ወደ 20። ስንደውልም ስልካቸው አያነሱም የት እዳሉ አናቅም። አይተናል እዛነበርን በመኪና ጭነው ነው የወሰዷቸው ” ስትል ተናግራለች።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ በመጨረሻም፣ ለጉዳዩ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ያሳሰቡ ሲሆን፣ ለቅሬታቸው ምላሽ ለማግኘት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ወደ ዩኒቨርሲቲውና ትምህርት ሚኒስቴር ሙከራ ቢያደርግም ለጊዜው ስልክ አልተነሳም።

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት በሽር አብዱላሂ (ዶ/ር)፣ የተማሪዎቹን ቅሬታ በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡ ትላንት በጠየቅናቸው ወቅት ስለጉዳዩ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን ገልጸው ነበር።

ፕሬዜዳንቱ በወቅቱ ሁነቱን ሲያስረዱም፣ “ጉዳዩ ‘ፈተና በሁለተኛ ጊዜ የተቀመጡት ተማሪዎች ውጤታቸው ‘#ችቲግ’ ምልክት አለው’ በመባሉ ትምህርት ሚኒስቴር ሆልድ ስላደረገ ነው/” ነበር ያሉት።

(ጉዳዩን የምንከታተለው ይሆናል)

አጋራ

ተዛማጅ ልጥፎች

Leave a Comment

አንደበት

ለተጠቃሚዎች የቅርብ ጊዜ አካባቢያዊ እና ዓለም አቀፍ ዜና  በማቅረብ ለአንባቢዎች የተሟላ መድረክ የሚሰጥ ዜና ጣቢያ ለአንባቢ ምቹ በይነገጽ እና ሰፋ ያለ የዜና ምድቦች አማካኝነት እንደ ፖለቲካ, ቴክኖሎጂ, መዝናኛ, ስፖርት እና ሌሎችም ባሉ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ወቅታዊ ዜናዎችን ያቀርባል፡፡

ጋዜጣ

አዳዲስ ዜናዎች በቅድሚያ እንዲደርሶት ኢሜሎን በማስገባት ይመዝገቡ

የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

@2025 – All Right Reserved.  Powered by Ewenet Communication